ፀሐይ ለቤተሰብ የወላጅነት ት/ቤት
የልጆችዎን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚረዱ ትምህርቶችን
ከባለሞያዎች አሁኑኑ ያግኙ!
በራስ መተማመንን ለልጆች በማስተማር ልጆችን ትጉህ እና ስኬታማ እንዲሆኑ መርዳት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
በራስ የመተማመን ክህሎትን መገንባት
ብዙ ሰዎች በራስ መተማመን በተፈጥሮ የተሰጠ ፀጋ ነው ብለው ያስባሉ፣ ግን አይደለም፡፡ በራስ መተማመን ያለማቋረጥ የሚያድግ ክህሎት ነው። ያለማቋረጥ ስንል ያለማቋረጥ መሞከር፣ ያለማቋረጥ መውደቅ፣ ያለማቋረጥ መነሳት፣ ያለማቋረጥ መማር ማለት ነው። በራስ መተማመን ልዩ የሚያደርገው ሁሉንም ሰው ከሚያመሳስለው ነገር መጀመሩ ነው።
ቁጣ ተፈጥሯዊ እና በአግባቡ ከገለጽነው ጤናማ ስሜት ነው። የቁጣ ስሜት ሲሰማን በአግባቡ ማስተናገድ መቻል ትልቅ ክህሎት ሲሆን ልምምድም ይጠይቃል።
ቁጣን በአግባቡ የማስተናገድ ብቃት ማዳበር
ሁሉም ሰው አንዳንዴ ይናደዳል! ቁጣ ለሰው ልጅ ራስን ለመጠበቅ እና ለመከላከል ወሳኝ ውስጣዊ ስሜት ነው፤ ገንቢ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ሰዎች እራሳቸውን እና ሌሎችን ለመጠበቅ እና ኢፍትሃዊነትን ለመቋቋም ጥንካሬ እና ድፍረት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።
የልጆችን ስሜት ለመለየት እና በነሱ ቦታ ሆነን ነገሮችን ለመረዳት ማህበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርትን መማር ወሳኝ እንደሆነ ያውቃሉ?
ማህበራዊና ስሜታዊ ልህቀትን ማስተማር
መልካም የሆነ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነትን ጥቅም ማወቅ፣ ከባድ ሁኔታዎችን የሚቋቋሙ እና ደስተኛ ልጆች እንዲኖርዎት እንደሚረዳ ያውቃሉ?
መልካም የሆነ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነት መፍጠር
ጤናማ ግንኙነት የሚመሠረተዉ እንዴት ነው? ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረንስ ዕድለኞች መሆን አለብን? በጭራሽ! ግንኙነትን የመገንባት ክህሎት በጊዜ ሂደት የሚማሩት እና ተግባራዊ የሚያደርጉት ነገር ሲሆን፣ ጠንካራ ግንኙነትን መመስረትን ከሁለቱም ወገን ትጋትን እና የማያቋርጥ ጥረት ማድረግን ይፈልጋል።
የአዕምሮ ቁስለት ለአንድ ጊዜ የሚፈጠር ሳይሆን በአዕምሯችን ውስጥ የማይታይ ምልክትን ጥሎ የሚያልፍ ክስተት መሆኑን ያውቃሉ?