የጥበብ ልጆችን ይተዋወቁ

የጥበብ ልጆች፡ ዓለም አቀፋዊ የተስፋ ምልክት (ብራንድ) ርህሩኋ ልጅ፣ ብልኋ ልጅ እና ኃይለኛዋ ልጅ ልዕለ-ኃያልነታቸውን ሲያዋህዱ የሚያቆማቸው ምንም ነገር አይኖርም።

ፍቅር

ርህራሄ የተሞላው ልብ ያላት የዋህ መንፈስ ነች። ሃሳባችሁን ስታደምጥ እና ስሜታችሁን ስትረዳ፣ በልብ-ለልብ ግንኙነት ከርቀት የማድመጥ (የቴሌፓቲ) ተሰጥዖዋ ከእናንተ ጋር ጥልቅ ትስስር እንድትፈጥር ያደርጋታል። 

ፍትሕ

ልበሙሉና እና ጠንካራ የሆነችዋ ፍትሕ፣ ሌሎችን በፍትሕ መንገድ ትመራለች። በመብረር ችሎታዋ፣ ከእንቅፋቶች በላይ ከፍ ብላ በመብረር ለትክክለኛው ነገር ትፋለማለች።

ትዕግስት

የትዕግስት እና የማሰብ ችሎታ ባለቤት ስትሆን፣ አስደናቂ የትንታኔ ችሎታዎችም አሏት። ጊዜን ለማቆም ባላት ኃይል፣ በፍጥነት መረጃን በየብልታቸው ትከፋፍላለች፣ ምስጢሮችንም በሚያስደንቅ ትክክለኛነት ትፈታለች።

የጥበብ ልጆችን ይመልከቱ

ክፍል 1: የእርዳታ ጥሪ 

አንዲት ወጣት ቤተሰቦቿ የወር አበባን በተሳሳተ መንገድ በመረዳታቸው ከቤት ስትጠፋ፣ የጥበብ ልጆች ሊያድኗት ይመጣሉ፣ ከፍቅር አያት መጠጊያ እና ጥበብን እንድታገኝም ይረዷታል። ለምለም የገጠማትን ተግዳሮት ለመጋፈጥ ድፍረትን ታገኛለች፣ በባህል እና በዘመናዊነት መሀል ያለውን ውስብስብ መንገድ ሲጓዙ፣ ጓደኛሞቹ በመካከላቸው ያለውን ትሥሥር ያጠናክራሉ።

Write your awesome label here.

ክፍል 2፦ ለእውነት በጽናት መቆም

የለምለም እናት በንዴት በመጦፏ ለምለም ጥበብ ልጆች ዘንድ ጥገኝነት እንድትፈልግ ትገደዳለች። ፍትሕ ለታማሚ ወንድሟን መድኃኒት ለማግኘት ስትጣደፍ፣ ገንዘብ ያበደረችውን አጎቷን ትጋፈጣለች። ለምለም በሁኔታው በመነቃቃት፣ እናቷ የወር አበባን በተመለከተ ያላትን የተሳሳተ ተለምዶአዊ አመለካከት ለመጋፈጥ ድፍረት ታገኛለች። ምንም እንኳን ከብዙ ክርክር በኋላ ዕርቅ ቢያወርዱም፣ ፍትሕ አጎቷ በእሷ ላይ የማይገባ ክስ ሲያቀርብ አዲስ ችግሮች መጋፈጥ ትጀምራለች።

Write your awesome label here.

ክፍል 3: ሐቀኝነት 

የጥበብ ልጆች የዕርዳታ ጠሪ ሲደርሳቸው ፍትሕ አጎቷ እያደረገ ስላለው ማታለል ያለበት የመሬት ውል ለጓደኞቿ ትነግራለች። ወደ ሩቅ መንደር በፍጥነት በመብረር፣ ደፋሯን ቦጌ ያገኟታል፣ ከመጠለፍም ያድኗታል። የቦጌ እህት መልካም የሴት ልጅ ግርዛት (ኤፍጂኤም) ባስከተለባት ችግር ውስጥ እንደሆነች ሲረዱ፣ የጥበብ ልጆች እህትማማቾቹ ይህንን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለመፋለም የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ ቃል ይገባሉ። ነገር ግን ቦጌ ይህንን ለማድ በመቃወም በአደባባይ ስትናገር ያንን ያልወደዱ ሰዎች ቤቷን ሊቃጥሉ ይሞክራሉ፣ የጥበብ ልጆችም ይህንን አደጋ ሊያስቆሙ ትግል ይጀምራሉ።

Write your awesome label here.

ክፍል 4: ችግርን የመቋቋም ችሎታን ማዳበር

በቦጌ በት ላይ የደረሰን ቃጠሎ ተከትሎ፣ ሙና፣ መናልባትም አሁንም በአካባቢው የሴት ልጆችን ግርዛት በምትፈጸመዋ ሴት፣ መጠለፏ ይታወቃል። ትዕግስት ፍለጋውን ስትመራ ፍንጮች ወደሙና አጎት መንደር ይጠቁማሉ። ወደ ቤት ሲመለሱ ትዕግስት ፍንጮቹን አንድ ላይ እንዴት እንዳሰባሰበች እና እንደተረዳች ትናገራለች፣ የጥበብ ልጆችም አሳዛኙን ሁኔታ ለማስቀረት ያደረጉትን የቡድን ሥራቸውን ስኬት ያከብራሉ።

Write your awesome label here.

ክፍል 5: ችግር የመፍታት ብቃትን ማዳበር

ሙና ምናልባትም በከተማዋ የመጨረሻዋ የሴት ገራዥ በሆነችው ሴት ከታፈነች በኋላ፣ የጥበብ ልጆች ልበሙሉነት የተሞላውን የምርመራ ሄደት ይመራሉ። በመንገገዳቸው ላይ መሰናክሎች ይገጥሟቸዋል እነሱ ግን ተስፋ አይቆረጡም።

ክፍል 6: የሚና አርዓያዎች

ለትምህርት ቤት የቡድን ፕሮጀክት፣ ፍቅር አባቱ ከበደ በቤት ውስጥ የኃይል ጥቃት ከሚያደርሰው ከጀማል ጋር ትመደባለች። የጥበብ ልጆች ከበደ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ጣልቃ ሲገቡ ጀማል በፍቅር ላይ ጉዳት ያደርሳል። ርዕሰ መምህሩ ለጀማል ሌላ እድል ቢሰጡም የከበደ ቁጣ ግን ቤተሰቡን አደጋ ላይ መጣሉን ይቀጥላል።

ክፍል 7: በቃ!

የከበደ ቁጣ በጀማል ላይ አካላዊ ድብደባ ያደርሳል። የጥበብ ልጆችም ጣልቃ በመግባት ጥቃቱን ሲያስቆሙ ከበደ ራሱን ይስታል። ቆይቶ፣ ጀማል በትምህርት ቤት ውስጥ እገዳ ይጣልበታል፣ ወደ ቤቱ መመለሱም ሌላ ግጭትን እንዲጋፈጥ ያደርገዋል።

ክፍል 8 የባህል ወጥመድ

ወዳጆ እና የመንደሩ አለቃ ሽሽግ የፍትሕን ሞግዚትነት እና የመሬት ባለቤትነቷን እንድትተው ያስገድዷታል። በተለየ አጋጣሚ፣ የጥበብ ልጆች በአስደናቂ ሁኔታ እስኪያድኗት ድረስ ሃና የግዳጅ ጋብቻን ትጋፈጣለች። ነገር ግን ሜቅደስ የሽሽግኝ ዳስ በማፍረስ የበቀል እርምጃ ትወስዳለች።

ክፍል 9: ሰርጉ

ፍትህ ወንድሞቿ እና እህቶቿ የአጎቷን የወዳጆን ቤት ትተው እንዲወጡ ለማሳመን ትታገላለች። በእቅዳቸው መሠረት ፍቅር እና እዕግስትን ሳትገናኝ ስትቀር ሁለቱ ፍትሕን ፍለጋ ይጀምራሉ፣ በመጨረሻም ጀማል እና ሽሽግ በሚደበቁበት የተከለከለ ዋሻ ውስጥ ያገኟታል። ሃናን ለማግኘት ማድረግ የነበረባቸው ፍላጎት እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ ነበረበት።

ክፍል 10: ራእይ

መቅደስ ሰርጉን እንድትደግስ ግፊት ሲደርስባት፣ ትዕግት የነፃ ትምህርት ዕድል ታገኛለች። ነገር ግን ያንን ትምህርት ለመከታተል መሄድ ማለት ከጓደኞቿ ፊትን ማዞር ሆኖ ይሰማታል። የወዳጆ ምስጢራዊ ዕቅድ ሲጋለጥ፣ የቤተሰብ ታማኝነት ፈተና ውስጥ ይወድቃል።

ክፍል 11: ፊት ለፊት

ሃና በአክስቷ እርዳታ ጋብቻዋን ትተዋለች። ትዕግስት ስላገኘችው ነጻ የትምህርት ዕድል ከእናቷ ጋር ሙግት ውስጥ ትገባለች። መቅደስ በድንገት ሠርጉን እንደሰረዘች ስትናገር፣ የሃና አክስት እውነትን እስከምትደርስበት ድረስ ጥርጣሬ ውስጥ ትገባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ናቲ ወንድም እና እህቶቹን ለመንከባከብ ትምህርቱን መሥዋዕት ያደርጋል። 

ክፍል 12፦ ከትናንት በስቲያ

አቤልና ሰላም በወንዝ ውስጥ መውደቃቸው የወዳጆን ቸልተኝነት ያጋልጣል፣ አስፈሪ ቀውስም ይከተላል። ገላን አስተማሪዋ ጥቃት ካደረሰባት በኋላ ከትምህርት ቤት የመባረር አደጋን ትጋፈጣለች፣ የጥበብ ልጆች ግን የእሷን ጉዳይ በእጃቸው ያስገቡታል። ወንድም እና እህትማማቾች በግጋፈጡት የደህንነት ስጋት ምክንያት የነፃ ትምህርት ህልሞች ከሳይንሳዊ የማወቅ ጉጉት ጋር ይደበላለቃሉ።

ክፍል 13: ድል!

በአንድነት፣ የጥበብ ልጆች ርዕሰ-መምህሩን በማስገደድ የገላን አስተማሪን ብልሹ ምግባር የሚያጋልጥ ማስረጃ በመግለጥ የገላንን ንጽሕኛ ያረጋግጣሉ። ወሳኝ በሆነ የሞግዚትነት ችሎት ውሎ ላይ፣ ኃይለኛ ምስክሮች የወዳጆን ብቃት-አልባነት ያጋልጣሉ፣ በመጨረሻም በጓደኛሞቹ ልበሙሉነት አማካኝነት ፍትሕ የወንድሞቿን እና የእህቶቿን ሞግዚትነት በማግኘት ፍትህ ያሸንፋል።