Write your awesome label here.

እንኳን ደህና መጡ
ትምህርት አንድ፡ የለምለም ልበሙሉነት፤የእርዳታ ጥሪ

እንደ ወላጆች፣ ሁላችንም አንድ የጋራ ፍላጎት አለን፦ የሕይወትን ተግዳሮቶች በጸጋ እና በድፍረት ማስተናገድ የሚችሉ በራስ የመተማመን እና የመቋቋም አቅም ያላቸው ልጆችን ማሳደግ። ይሁን እንጂ፣ ፍርሃት እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ብዙውን ጊዜ ልጆቻችን ትግላቸውን እንዳያጋሩን እና የሚፈልጉትን ድጋፍም እንዳይጠይቁን እንቅፋት ይፈጥራሉ።

"የለምለም ልበሙሉነት" የተባለውን፣ ግልጽ በሆነ በነጻ ተግባቦት እና ርህራሄ ኃይል አማካኝነት በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማጎልበት የተቀየሰውን ሥርነ-ቀል ኮርስ ማስተዋወቅ። የወር አበባን እንደ ነውር በሚያይ ማህበራዊ አመለካከት ምክንያት ያጋጠማትን ተግዳሮት ለመጋፈጥ በምትታገል ለምለም በምትባል ልጃገረድ የልበሙሉነት ጉዞ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይህ ኮርስ፣ ድንቅ የአተራረክ ብቃትን፣ በይነተገናኝ ተሳትፎን እና ስለሰው ተሞክሮ ጥልቅ ግንዛቤን አጣምሮ ይዟል።

ተግዳሮቱ፦

በማህበረሰባችን ውስጥ፣ የሰውነት ሕዋሳዊ ለውጦችን የመሳሰሉ አንዳንድ ርዕሶች ብዙውን ጊዜ በሀፍረት እና በተሳሳተ አመለካከቶች ተሸፍነዋል፣ ይህም በአዳጊ ልጆች ዘንድ ፍርሃትን እና ጭንቀትን ያስከትላል። ይህ ፍርሃት፣ የሚያስፈልጋቸውን እገዛ ከመሻት ሊከለክላቸው እና ጥበብ የጎደለው ምርጫ እና ራሳቸውን ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ በሚገፏቸው ስጋጎች ላይ ሊጥላቸው ይችላል። ነገር ግን፣ የለምለም ጉዞ ስለእሷ ብቻ አይደለም። ስለ እርስዎ እና ስለ ቤተሰብዎም ጭምር ነው። 

መፍትሔው፦

"የለምለም ለበሙሉነት" ነጻ ለሆነ ውይይት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍርድ የማይሰጥ ቦታን ይሰጣል፣ በዚም በቅድመ-አስሮች እና በአስሮች የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊዎችዎ ያለፍርድ በሕይወት ውስጥ የሚገጥሟቸውን ፍርሃታቸውን እና ስጋታቸውን እንዲገልጹ ያስችላቸዋል። በበይነተገናኝ ትምህርቶች፣ በባለሙያ መመሪያዎች እና በአሳታፊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ከልጅዎ ጋር ጠንካራ እና የማይበጠስ ትስስር በመፍጠር በደግነት፣ በርህራሄ እና በመረዳት ስሜት እንዴት ምላሽ መስጠት እንደምችሉ ይማራሉ።

እቅዱ:-

ለ"የለምለም ልበሙሉነት" ኮርስ ይመዝገቡ እና የምከተሉትን ጥቅሞች ያግኙ፦
  • በስሜታዊ ብልህነት፣ በተግባቦት ክህሎቶች እና በወላጅ-ልጅ መስተጋብር ላይ በይነተገናኝ ትምህርቶች፣

  • ኤክስፐርት-መር ዌቢናሮች እና የጥያቄ እና መልስ ስብሰባዎች ከሳይኮሎጂስቶች፣ አስተማሪዎች እና ከግንኙነት ስፔሻሊስቶች ጋር፣
  • ርህራሄን፣ አካታችነትን እና ባህላዊ ግንዛቤን በሚያበረታቱ እንቅስቃሴዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ መሳተፍ፣

  • ተሞክሮዎችን ማጋራት እና ድጋፍ መፈለግ የሚችሉበት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው ወላጆች ሕይወት የተሞላው የመስመር ላይ ማህበረሰብ፣ 
  • ልዩ የተረት ነገራን፣ የተለያዩ የባህል ውክልናዎችን እና ዓለም አቀፋዊ እይታን የሚያሳዩ የአፍሪካ ልዕለ ኃያል ተከታታይ ፊልሞችን ማጣጣም፣ 

ስለዚህ፣ ምን ይጠብቃሉ? በዚህ የልበሙሉነት እና ራስን የማወቅ ጉዞ ላይ እኛን ይቀላቀሉ።
አባል ይሁኑ። አሁን ይመዝገቡ።