Write your awesome label here.

የቦጌ ፍልሚያ፤ ሐቀኝነት

ትምህርት ሶስት

የማይገታ የመልካምነት ኃይል ለመሆን ጊዜው አሁን ነው! እንደ ወላጆች፣ ሁላችንም የሕይወትን ተግዳሮቶች በድፍረት ማሸነፍ የሚችሉ ጠንካራ እና ችግርን ተቋቋሚ ልጆችን ማሳደግ እንፈልጋለን። እውነታው ይህ ነው፦ በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች እኛ በእነሱ እድሜ ብንሆን ልናስባቸው የማንችላቸውን ከለከፋ ወይም ጉልበተኝነት እስከ የእኩዮች ተጽዕኖ እንዲሁም የልጃገረዶችን ክብር የሚያጎድፉ እንደ ሴት ልጆች ግርዘት (ኤፍጂኤም) ያሉ የፍትሕ መጓደል ያጋጥማቸዋል። ለዚያም ነው "የቦጌ ፍልሚያ - ኮርስ ሶስት፡- ሐቀኝነት" ቤተሰብዎን ለማጎልበት የግድ ልወስዱት የሚገባ ኮርስ የሆነው። ችግርን ለመቋቋም የሚችሉ ወጣቶችን ለማሳደግ ቁልፉ ምንድነው? ሐቀኝነት። በቦጌ፣ በመልካም እና በልበሙሉዎቹ የጥበል ልጆች ስሜት የሚይዝ ታሪክ አማካኝነት ይህ ኮርስ ቤተሰብዎ የሚከተሉትን እንዲያደርግ ያስችለዋል:-

በዚህ ኮርስ ውስጥ በምታገኙት የቦጌ፣ የመልካም እና የልበሙሉዎቹ የጥበብ ልጆች መሳጭ ታሪክ፣

የምያገኙት፦

  • በሐቀኝነት ጥንካሬ: እውነተኛ ስሜትዎን መቀበል ጠንካራ እንድሆኑና ከሌሎች ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት እንድመሠርቱ እንዴት ሊረዳዎት እንደሚችል ይወቁ። ልበሙሉዎቹ የጥበብ ልጆች፣ ሐዘናቸውን እና ሰቆቃቸውን በግልጽ ሲገልጹ፣ እውነተኛ ጥንካሬም የሚገለጸው በስሱነት (በተጋላጭነት ስሜት) ውስጥ መሆኑን ሲያሳዩ ከእነሱ ይማሩ።

  • የርህራሄ ትስስር፡ በዙሪያዎ ካሉ ሰዎች ጋር ትርጉም ያለው ትስስር በመፍጠር ረገድ የርህራሄን ኃይል ይለማመዱ። እውነተኛ ስሜትን መግለጽ እንዴት መረዳትን እና ርህራሄን እንዴት እንደሚያበረታታ፣ ግንኙነቶችዎን እንደዴት እንደሚያበለጽግ እና የቤተሰብዎን አንድነት እንዴት እንደሚያጠናክሩ ያስሱ።

  • የመምራት ተነሳሽነት: ቦጌ ኢፍትሃዊነትን በማያወላውል ድፍረት እና ርህራሄ ስትጋፈጥ እና ለለውጥ ስትሟገት በማየት በሷ ድርጊት ይነቃቁ። ርኅራኄ ማሳየት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንድወስዱና መከራ ቢደርስብዎም እንኳ ትክክል ለሆነው ነገር እንድቆሙ ሊያነሳሳዎ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ይማሩ።ይህ መሳጭ ኮርስ እነዚህን እውነተኛ የአመራር መርሆዎች ወደ ሕይወት ለማምጣት ቪዲዮዎችን፣ እንቅስቃሴዎችን እና ጨዋታዎችን ያካትታል።

ሐቀኛነትን ለመቀበል ዝግጁ ነዎት?

የቤተሰብዎን ትስስር ለማጠናከር እና በዓለም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማድረግ ይህ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎት።
 አሁን ይመዝገቡ! አባል ይሁኑ።